All Posted News and Events

Posted date:- 2026-07-03 08:54:28         Back To Main Page

በወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የመንግስት ሰራተኞች ቆጠራ መካሄድ ጀመረ፡፡ ደሴ፡- ሰኔ 26 / 2018 ዓ.ም (ወስፖኮ) የወይዘሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የሰው ኃይል አስተዳደርን ይበልጥ ግልጽ፣ ዘመናዊና ውጤታማ ለማድረግ ያለመ የመንግስት ሰራተኞች ቆጠራ ሂደት ትናንት ተጀመረ፡፡ ይህ ክልል አቀፍ ሰራተኞችን የማጥራትና የመቁጠር ስራ በይፋ ከመጀመሩ አስቀድሞ፣ ሂደቱ ስኬታማ እንዲሆን ለተቋሙ ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሂዷል። በውይይቱም ላይ የቆጠራው ዋና ዓላማ፣ አስፈላጊነትና በሂደቱ ወቅት ሰራተኞች ማሟላት የሚገባቸውን ተያያዥ ሰነዶች በተመለከተ ዝርዝር ማብራሪያ ተሰጥቷል። ይህ የሰራተኞች ቆጠራ በዋናነት የመንግስትን የሰው ኃይል መረጃ በአግባቡ ለመያዝ፣ ሰራተኞች መኖርና አለመኖራቸውን ለማረጋገጥ እንዲሁም የተቋሙን የሰው ኃይል ስምሪት ከኮሌጁ የልማትና የትምህርት ዕቅዶች ጋር ለማጣጣም ትልቅ ፋይዳ አለው። ከትናንት ጀምሮ በይፋ የተጀመረው ይህ የቆጠራ ሂደት ሁሉንም ቋሚ የመንግስት ሰራተኞችን የሚያካትት ሲሆን፣ ሂደቱ በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳና መመሪያ መሰረት በጥንቃቄ እንዲጠናቀቅ ኮሌጁ አስፈላጊውን ዝግጅት በሙሉ ማጠናቀቁ ታውቋል። ሰራተኞችም ሂደቱን በትዕግስትና አስፈላጊውን መረጃ በወቅቱ በመስጠት እንዲተባበሩ ጥሪ ቀርቧል።

..........................................................................................................................................

Posted date:- 2026-06-24 09:58:01         Back To Main Page

የቅሬታ ሰሚ አተገባበር እና ተግባራዊነትን በተመለከተ ለቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ አባላት ስልጠና ተሰጠ፡፡ ደሴ፡- ሰኔ 15 / 2018 ዓ.ም (ወስፖኮ) በወይዘሮ ስኂና ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የቅሬታ ሰሚ አተገባበር እና ተግባራዊነትን በተመለከተ ለኮሌጁ የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ አባላት ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ ስልጠናው በEASE (Education and Skill For Employability) ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ የተዘጋጀ ነው፡፡ ስልጠናውን የሰጡት የEASE ፕሮጀክት የአካባቢና ማህበራዊ ጥበቃ (Environment & Social Safeguard) አስተባባሪ አቶ መላኩ መሃመድ ሲሆኑ፣ በፕሮጀክቱ ሂደት ውስጥ ቅሬታዎች ቢፈጠሩ ሊከተሉ ስለሚገባቸው የቅሬታ አፈታት ሂደቶች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ አስተባባሪው አክለውም እስካሁን በፕሮጀክቱ ዙሪያ የተነሱ ቅሬታዎች ምን ምን እንደነበሩና በተግባር የተፈቱበትን ስኬታማ መንገድ ለኮሚቴው አባላት አስታውሰዋል፡፡ በስልጠናው ወቅት የስነ-ምግባር ደንብ፣የአካባቢ ጥበቃ ትኩረት እንዲሁም በEASE ፕሮጀክት አማካኝነት በስርዓተ-ፆታ ዙሪያ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን በተመለከተ ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን፣ በተለይም በሴቶች አቅም ግንባታ ዙሪያ ወደፊት በርካታ ስራዎችን ለመስራት መታቀዱንም ተገልጿል፡፡ በመጨረሻም የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ አባላቱ በEASE ፕሮጀክት ድጋፍ በኮሌጁ ግቢ ውስጥ ለሴት ሰልጣኞች ማረፊያና (Female Trainees Wellness center) የንፅህና መጠበቂያ እንዲያገለግሉ ተለይተው የተዘጋጁትን ክፍሎች በመዘዋወር ጎብኝተዋል፡፡

..........................................................................................................................................

Posted date:- 2026-01-13 07:44:18         Back To Main Page

ወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለአራት ወራት ያሰለጠናቸውን የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ሰልጣኞችን ዛሬ አስመርቋል፡፡ ደሴ፡- ጥር5/2018 ዓ.ም (ወስፖኮ) በፍቅር ኢትዮጵያ ብሔራዊ የአዕምሮ እድገትና ውስንነት ማህበር ደሴ ቅርጫፍ ድጋፍ አማካኝነት በወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በዶሮ እርባታ ሲሰለጥኑ የነበሩ 10 የአዕምሮ ውስንነት ያለባቸው ሰልጣኞችን ዛሬ አስመርቋል፡ ፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሞን ይመር ወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከደሴ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት መምሪያ ጋር በጋራ በመሆን ለበርካታ ስራ አጥ ወጣቶች መሰል ስልጠናዎችን እየሰጠ መሆኑን ገልፀው የዛሬው ተመራቂዎች ግን ለየት የሚያደርገው በኮሌጁ እንዲህ አይነት ስልጠናዎች ተሰጥተው የማያውቁ በመሆናቸው ጥሩ ልምድ የተገኘበት ነው ብለዋል፡፡ አቶ ሰለሞን አክለውም ምንም እንኳን የተለያዩ የጤና እክሎች ቢኖርም ማንኛው ሰው ስልጠና ከወሰደና በቂ ድጋፍ ካገኘ መስራት እንደሚቻል ማሳያ ናችሁ ብለዋል፡፡የሰለጠናችሁበት ዘርፍ ሰፊ የገበያ እድል ያለበት በመሆኑ እድሉን በአግባቡ ለመጠቀም የቤተሰቦቻቸው እገዛ እንዳይለያቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በፍቅር ኢትዮጵያ ብሔራዊ የአዕምሮ እድገትና ውስንነት ማህበር ደሴ ቅርጫፍ ሰብሳቢ አቶ መለሰ በላይ ማህበሩ ከተመሰረተ 17 ዓመታትን ማስቆጠሩን ጠቁመው የተመሰረተበት ዓላማ የአዕምሮ እድገትና ውስንነት ያለባቸው ልጆች ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ ታሳቢ በማድረግ ነው ብለዋል፡፡ ከደሴ ከተማ ስራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ አቶ አብዱልሀሚድ መሀመድ በበኩላቸው ተመራቂዎቹ ቶሎ ወደ ስራ ይገቡ ዘንድ መምሪያው አስፈላጊውን ትብብር እንደሚያደርግ ጠቁመው የብድር አቅርቦቱን ማፋጠን፣ የስራ ቦታ ማመቻቸት እንዲሁም የገበያ ትስስር በመፍጠር በኩል ለተመራቂዎቹ በልዩነት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡ በዕለቱ በዶሮ እርባታ ዘርፍ ውጤታማ የሆኑ ግለሰብ ተገኝተው ለተመራቂዎቹ ልምዳቸውን አካፍለዋል፡፡ በመጨረሻም ለሰልጣኞቹ ሰርተፊኬት የተሰጠ ሲሆን የሰልጣኞቹ ቤተሶችም ለአሰልጣኞቻቸው የምስጋና ሜዳልያ በመስጠት ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡

..........................................................................................................................................

Posted date:- 2026-01-06 08:29:51         Back To Main Page

የኮሌጁ ኢንዱስትሪ አድቫይዘሪ ቦርድ በኮሌጁ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ጎበኙ፡፡ ደሴ፡ታህሳስ 28/2018ዓ.ም (ወስፖኮ) የወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የኢንዱስትሪ አድቫይዘሪ ቦርድ አባላት በEASE ፕሮጀክት ድጋፍ በኮሌጁ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ጎብኝተዋል፡፡ የቦርዱ አባላት በኮሌጁ የተዘረጋውን የአይሲቲ መሰረተ ልማትን ጨምሮ በፕሮጀክቱ የተቋቋመውን የቅሬታ ማስተናገጃ ቡድን በኩል እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ጎብኝተዋል፡፡ በኮሌጁ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት የሚበረታቱ ናቸው ያሉት የቦርዱ አባላት በቀጣይ ስራዎቹ ወጥነት ባለው መልኩ ይቀጥሉ ዘንድ በትጋት መስራት እንደሚገባና የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ ገልፀዋል።

..........................................................................................................................................

Posted date:- 2026-01-06 08:17:57         Back To Main Page

ለኮሌጁ አስተዳደር ሰራተኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ፡፡ ደሴ፡ታህሳስ 28/2018ዓ.ም (ወስፖኮ) በወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በEASE ፕሮጀክት ድጋፍ ለኮሌጁ አስተዳደር ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ፡፡ ስልጠናውን የከፈቱት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሞን ይመር ስራዎች በተገቢው መልኩ በእውቀት ተደግፈው እንዲሰሩ ለባለሙያዎች በተለያየ ጊዜ ሙያቸውን መሰረት ያደረገ የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት አስፈላጊ በመሆኑ ስልጠናው ተዘጋጅቷል ብለዋል፡፡ ስልጠናው ከደሴ ከተማ አስተዳደር ሲቪል ሰርቪስ መምሪያ በመጡ ባለሙያና በኮሌጁ የአይሲቲ ትምህርት ዘርፍ አስተባባሪ በኩል የተሰጠ ሲሆን ስልጠና በሲቪል ሰርቪስ የሰው ኃይል ስራዎችና በዲጂታል ሊትረሲ ላይ ያተኮረ ነው፡፡ በስልጠናው የኮሌጁ የሰው ኃይል፣ የሬጅስትራር፣ የላይብረሪ፣ የቢሮ ፀሃፊዎች፣ የቅሬታ ሰሚ እንዲሁም የህዝብ ግንኙነት ባለሙዎች ተሳትፈዋል፡፡

..........................................................................................................................................

Posted date:- 2025-12-12 09:05:37         Back To Main Page

ለጥበቃና ጽዳት ሰራተኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡ ደሴ፡-ታህሳስ3 /2018 ዓ.ም (ወስፖኮ) በEASE Project ድጋፍ በወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለሚሰሩ ለጥበቃና ጽዳት ሰራተኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡ በስልጠናው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሞን ይመር አንድ ተቋም እያደገ ይሄድ ዘንድ ጥሩ መዋቅር፣ጥሩ ቴክኖሎጂና የሰው ሃብት የተሟላ ሊሆን ይገባል፡፡ስለሆነም የዚህ ስልጠና ዓላማ የተቋሙን የእድገት ሁኔታ ማሳለጥ በመሆኑ ይህ እውን ይሆን ዘንድ በተቋሙ ውስጥ ያሉ ሰራተኞች ስራቸውን በተመለከተ እውቀትና ክህሎት ሊኖራቸው ስለሚገባ ይህ ስልጠና ተዘጋጅቷል ብለዋል፡፡ ስልጠናው ነገም የሚቀጥል ይሆናል፡፡

..........................................................................................................................................

Posted date:- 2025-12-09 05:56:23         Back To Main Page

የወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የአመራርነት ስልጠናና እዉቅና መስጫ ማዕከል (Leadership Development and Certification Center) ከኢትዮጵያ አቬሽን ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ በመሆን በ EASE Project ድጋፍ በአራት ሞጁሎች ላይ ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡ ደሴ፡-ህዳር 24/2018 ዓ.ም (ወስፖኮ) በስልጠናው መክፈቻ ላይ የተገኙት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሞን ይመር የዚህ ስልጠና ዋና ዓላማ የአመራር ክህሎትን ማሳደግ፣ የተቋም አፈፃፀምና ምርታማነትን ማሳደግ እንዲሁም የሰራተኞችን ተሳትፎ ማሳደግ በመሆኑ ሁሉም ተሳታፊ ስልጠናውን በትኩረት በመከታተል ለውጤታማነት መትጋት ይገባል ብለዋል፡፡ ይህ ስልጠና በወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለሚገኙ የቡድን መሪዎች፣ የማኔጅመንት አባላት፣ የዲፓርትመንት ተጠሪዎች እንዲሁም ከክላስተር ኮሌጆች የመጡ ዋና ዲኖች እና ለደሴ ከተማና ለደቡብ ወሎ ስራና ክህሎት መምሪያ የት/ትና ስልጠና ቡድን መሪዎች እየተሰጠ ነው፡፡ ስልጠናው ተቋማዊ አመራር፣ የምርት አስተዳደር፣ ዲጂታላይዜሽንና የአስተዳደር ለውጥ በሚሉ አራት ጉዳዮች ላይ ያተኩራል፡፡

..........................................................................................................................................

Posted date:- 2025-12-09 05:55:16         Back To Main Page

የስልጠና ማስታወቂያ ====== የወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የሜታል ማኑፋክቸሪንግ ትምህርት ዘርፍ በሚከተሉት የስልጠና ሙያዎችን በመደበኛና በአጫጭር ማሰልጠን ይፈልጋል።

..........................................................................................................................................

Posted date:- 2025-11-27 07:50:41         Back To Main Page

ከአማራ ልማት ማህበር ደሴ ኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ብቁ ወጣት በሚል ፕሮግራም ከደሴ ከተማ ለተውጣጡ ስራ ፈላጊ ወጣቶች ስልጠና በወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ እየተሰጠ ነው፡፡ ስልጠናው ለ30 ቀናት የሚቆይ ሲሆን በልብስ ስፌት እንዲሁም የቤት ውስጥ የውሃ መስመርና የስነ-ንፅህና መስመር ዝርጋታ ዙሪያ ያተኮረ ነው፡፡

..........................................................................................................................................

Posted date:- 2025-10-29 02:02:12         Back To Main Page

በወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለአዲስ ተመዝጋቢ ሰልጣኞች የሳይኮሜትሪክ ቴስት እየተሰጠ ነው፡፡ ደሴ፡-ጥቅምት19/2018ዓ.ም(ወስፖኮ) ይህ የኦን ላይን ቴስት በሀገር አቀፍ ደረጃ በአዲስ መልክ እየተተገበረ ሲሆን ተማሪዎች ለወደፊት የሚሰለጥኑበትን የትምህርት ዘርፍ ለመምረጥ ያግዛቸው ዘንድ ተዘጋጅቷል፡፡ የሳይኮሜትሪክ ቴስቱ በ2018 የትምህርት ዘመን ኮሌጃችንን ለሚቀላቀሉ አዲስ ተመዝጋቢ ሰልጣኞች ከሰኞ ጀምሮ እየተሰጠ ነው፡፡ የሳይኮሜትሪክ ቴስቱ አዲስ ተመዝጋቢ ሰልጣኞች ከራሳቸው፣ከቤተሰቦቻቸውና ከጓደኞቻቸው ጋር ተመካክረው ለመምረጥ ከመጡት የትምህርት ዘርፍ በተጨማሪ የተማሪዎችን የስነ-ልቦና ችሎታዎች ማለትም የግንዛቤ፣የስብዕናና ያላቸውን ተሰጥኦ የሚያመላክታቸው በመሆኑ ለወደፊት ውጤታማ የሚሆኑበትን የትምህርት ዘርፍ እንዲወስኑ የሚረዳ ምክረ ሃሳብ ነው፡፡

..........................................................................................................................................

Posted date:- 2025-10-23 01:20:28         Back To Main Page

በሀገራችን ዘመናዊ ትምህርት ታሪክ ቀዳሚ የሆነው የወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ እንኳን ለ2018 የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ ይላል፡፡ ኮሌጃችን በ2017ዓ.ም በዓለም አቀፍ የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ISO 9001:2015ን ተግባራዊ በማድረጉ ከኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የጥራት ሥራ አመራር ሥርአት ሰርተፊኬት ማግኘቱን ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነው፡፡ በርካቶች ሰልጥነው የሙያ ክህሎት ባለቤት የሆኑበት ኮሌጃችን በተለያዩ የስልጠና አይነቶች፣ብቃት ባላቸው አሰልጣኝ መምህራን ፣በተለያዩ ቴክኖሎጂዎች በተደራጁ ወርክሾፖችና የኢንተርኔት አገልግሎት ያላቸው ቤተመፃሃፍቶችን በማደራጀት እያሰለጠነ ይገኛል፡፡ ዘንድሮም በ7 የስልጠና ዘርፎች አዳዲስ ሰልጣኞችን ከደረጃ1-5 በቀንና በማታ መርሃ-ግብር ለማሰልጠን ዝግጅቱን አጠናቆ ምዝገባ ጀምሯል፡፡ እርስዎ ባሉት የሙያ ዘርፎች ሰልጥነው ራስዎን፣ቤተሰብዎንና ሀገርዎን መጥቀም ከፈለጉ ያለምንም ጥርጥር ቀዳሚ ምርጫዎ ወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅን ያድርጉ!

..........................................................................................................................................

Posted date:- 2025-10-23 01:19:21         Back To Main Page

የኢፌድሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከአብክመ ባህልና ቱሪዝምና ከደሴ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ጋር በመተባበር በቆዳ ዘርፍ ለተሰማሩ ግለሰቦች የቴክኖሎጂ ሽግግርና የተግባር ስልጠና በወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ተሰጠ፡፡ ስልጠናው ለአምስት ተከታታይ ቀናት የተሰጠ ሲሆን 30 የሚሆኑ ሰልጣኞችም ተሳትፈው ሰርትፊኬታቸውን ተቀብለዋል፡፡

..........................................................................................................................................

Posted date:- 2025-10-10 02:31:12         Back To Main Page

የወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የአመራርነት ስልጠናና እዉቅና መስጫ ማዕከል(leadership development and certification center) ተቋቋመ። ደሴ፡-መስከረም 30/2017ዓ.ም(ወስፖኮ) የወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከኢትዮጵያ አቬሽን ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ በመሆን ስልጠና ለመስጠት ለማማከር ና ድጋፍ ለመስጠት የተቋቋመዉ ይህ ማዕከል ብቃት ያላቸዉ አመራሮችን በማፍራት ዉጤታማ ተቋም ለመፍጠር ይሰራል። በስልጠና መስጫ ማዕከሉ መክፈቻ ላይ የተገኙት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሞን ይመር ተቋማት ዉጤታማ ይሆኑ ዘንድ ጥሩ የአመራር ብቃት ያላቸው መሪዎች ሊኖሩት ይገባል።በመሆኑም ይህንን እዉን ለማድረግም ይህን ሴንተር መክፈት አስፈልጓል ብለዋል። በተጨማሪም ማዕከሉ ስልጠና ለሚፈልጉ ተቋማት በሚፈልጉት የአመራርነት ስልጠናና መሰል ጉዳዮች ዙሪያም ይሰራል። በመጨረሻም ስለማዕከሉ አጠቃላይ ገፅታ በማዕከሉ ዳይሬክተር አቶ ማስረሻ ጋሻው አማካኝነት ቀርቦ በወደፊት ስራዎች ዙሪያ ዉይይት ተደርጓል።

..........................................................................................................................................

Posted date:- 2025-10-01 02:19:20         Back To Main Page

የወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ2017ዓ.ም እቅድ አፈፃፀም ግምገማና የ2018 ዓ.ም እቅድ ትውውቅ አካሄደ። በመድረኩ የ2017 ዓ.ም እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በኮሌጁ እቅድና በጀት ክትትል ባለሙያ አቶ ብርሃን አበራ የቀረበ ሲሆን በጀት ዓመቱ በክልል ደረጃ በኮምቦልቻ ከተማ በተካሄደው የቴክኖሎጂ፣ የክህሎት፣ የተግባራዊ ጥናትና ምርምር እንዲሁም የስራ ፈጠራ ውድድር በድምር ውጤት 2ኛ በመሆን የሰርተፊኬትና የዋንጫ ተሸላሚ የሆነበት፣ በዓለም አቀፍ የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ISO 9001:2015 (QMS) ተግባራዊ በማድረጉ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የጥራት ሥራ አመራር ሥርአት ሰርተፊኬት የተሰጠበት እንዲሁም በክልል ደረጃ በአፈፃፀም 2ኛ ደረጃ በመሆን የእውቅናና የምስጋና የምስክር ወረቀት የተሸለመበትና የተለያዩ ተግባራትን ያሳካበት ዓመት እንደነበር በሪፖርቱ ተዳሷል፡፡ በተመሳሳይም በ2018 ዓ.ም ከትምህርትና ስልጠና፣ከኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ከአስተዳደር ስራዎች አንፃር ሊከናወኑ የታቀዱ ተግባራት በባለሙያው ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል፡፡ በተጨማሪም የEASE ፕሮጀክት የ11 ወራት የስራ አፈፃፀምና የቀጣይ አንድ ዓመት እቅድ በኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሞን ይመር ቀርቧል፡፡ በቀረበው ሪፖርትና እቅድ ዙሪያ ከተሳታፊዎች ለተነሱ የተለያዩ ሃሳቦች የኮሌጁ ዲኖች ምላሽ የሰጡ ሲሆን በምላሻቸውም የተነሱት ሃሳቦች ተገቢ መሆናቸውን ገልፀው በኮሌጁ የሚከናወኑና እየተከናወኑ ያሉት ተግባራት የሁሉንም እርብርብ የሚጠይቁ በመሆናቸው ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡

..........................................................................................................................................

Posted date:- 2025-07-09 08:52:11         Back To Main Page

የኮደርስ የምረቃ ስነ-ስርዓትና የአልባሳትና የፋሽን ትርኢት ተካሄደ፡፡ የወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የኮደርስ ስልጠና የሰለጠኑ ሰልጣኞች፣አሰልጣኞችና የአስተዳደር ሰራተኞችንም ዛሬ በደመቀ ሁኔታ አስመርቋል። የምረቃ ስነ-ስርዓቱን አስመልክቶ ንግግር ያደረጉት የወ/ሮ ስኂን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ምክትል ዲንና የትምህርትና ስልጠና አስተባባሪ አቶ ነፃነት አሳምነው ለተመራቂዎችን እንኳን ደስ አላችሁ ያሉ ሲሆን አለም የደረሠበትን ቴክኖሎጂ ላይ ለመድረስ የቴክኖሎጂ ክህሎትን ማዳበር አስፈላጊ በመሆኑ ኮደርስና መሰል ስልጠናዎች በመውሰድ እውቀትንና ክህሎትን ማሻሻል ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ በኮሌጁ በአራቱ የኮደርስ ስልጠናዎች ማለትም በአረቲፍሻል ኢንተለጀንስ ፣ አንድሮይድ ዲቨሎፐር፣ ዳታ አናላይሲስና ፕሮግራሚንግ ፋንዳሜንታል ስልጠናዎች በተከታታይ ድጋፍና ክትትል አማካኝነት ስልጠናውን ያጠናቀቁ ተመራቂዎች ተመርቀዋል። በዕለቱ በተመሳሳይም የአልባሳትና የፋሽን ትርኢት ተካሂዷል፡፡ ወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ስልጠና ከሚሰጥባቸው የስልጠና ዘርፎች መካከል አንዱ የሆነው የጨርቃጨርቅ እና አልባሳት የስልጠና ዘርፍ በቀዳሚነት ይጠቀሳል፡፡ ይህ ስልጠና ዘርፍ በኮሌጁ መሰጠት የጀመረው ከ1994 ዓ.ም ጀምሮ ነው፡፡ በወቅቱ በጨርቃ ጨርቅ (Textile) 25 እንዲሁም በአልባሳት ስራ (Garment) 25 በድምሩ 50 ሰልጣኞችን ተቀብሎ ማሰልጠን ጀመረ፡፡ አሁን ላይ በዚህ የስልጠና ዘርፍ ስር ስልጠና ከሚሰጥባቸው የሙያ ዓይነቶች መካከል የፋሽን ዲዛይን ሙያ አንዱ ነው፡፡ ይህ ሙያ ከሳይንሳዊ ፅንሰ-ሀሳቡ (Theory) ጀምሮ በተግባር የተደገፈ ስልጠና ይሰጣል፡፡በዚሁ የስልጠና ዘርፍ አማካኝነት በኮሌጁ የአልባሳትና የፋሽን ትርኢት ተካሂዷል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሞን ይመር ይህ የስልጠና ዘርፍ ከሌሎች ሙያዎች በተሻለ መልኩ ለፈጠራ ስራ የሚጋብዝ በመሆኑ ሰልጣኞች ብቃታቸውን እንዲያዎጡ የሚረዳ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ዘንድሮም ለሁለተኛ ጊዜ በተካሄደው የፋሽን ትርዒት ላይ 24 ሰልጣኞች የተሳተፉ ሲሆን ከእነዚህ መካከል አራት የመጀመሪያ አመት ሰልጣኞች የተሳተፉበት የአልባሳትና የፋሽን ትርኢት በደማቅ ሁኔታ ለታዳሚያን ቀርቧል፡፡ በዚህ የፋሽን ትርኢት መድረክ ላይ በኮሌጁ ዘመናዊ የወንድና የሴት አልባሳት ለእይታ ቀርበዋል፡፡በተለይም የእነዚህን አልባሳት ስራ ለየት የሚያደርገው ብዙዎቹ በማሰልጠኛ ወርክሾፖች ውስጥ የተሰሩ መሆ

..........................................................................................................................................

Posted date:- 2025-05-28 06:08:49         Back To Main Page

የወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለኢንዱስትሪ አድቫይዘሪ ቦርድ አባላትና ለኮሌጁ ማኔጅመንት አባላት በኮሌጁ እየተተገበረ ባለዉ EASE ፕሮጀክት የስራ አፈፃፀም ዙሪያ ግምገማ አካሄደ። ትምህርትና ክህሎት ለቀጣሪነት(EASE)ፕሮጀክት በኮሌጁ በተያዘው ዓመት ጀምሮ በመተግበር ላይ ሲሆን በፕሮጀክቱ እስካሁን የተከናወነውን የስራ አፈፃፀም አስመልክቶ የኮሌጁ ምክትል ዲንና የትምህርት ስልጠና አስተባባሪ አቶ ነፃነት አሳምነው አማካኝነት ሰነድ ቀርቦ ዉይይት ተደርጎበታል። በዉይይቱ ላይ ፕሮጀክቱ ብቃት ያለዉ ሰልጣኝ ለማፍራት አጋዥ መሆኑ ታስቦበት በጥሩ አፈፃፀም እየተተገበረ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በቀጣይም የፕሮጀክቱን የስራ አፈፃፀም የሚገመግም መሰል ዉይይት ሊደረግ ይገባል ተብሏል።

..........................................................................................................................................

Posted date:- 2025-05-28 10:06:13         Back To Main Page

የወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በሀገር ውስጥ ከሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችል ውይይት አካሄደ፡፡ በውይይቱ ላይ በትብብር ለመስራት ያመች ዘንድ ከኮሌጁ፣ከኢንዱስትሪዎችና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት የሚጠበቁ ተግባራትን አስመልክቶ በኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሞን ይመር አማካኝነት ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በውይይቱ ላይ ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የሚወጡ ሰልጣኞች ወቅቱን ያማከለ ዕውቀትና ክህሎት ይዘው እንዲወጡ በማስቻልና በተመሳሳይም የአሰልጣኞችን አቅም በመገንባት በኩል በትኩረትና በትብብር ሊሰራ እንደሚገባ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ በመጨረሻም ኮሌጁ ከኢንዱስትሮቹ ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡

..........................................................................................................................................

Posted date:- 2025-04-22 04:20:25         Back To Main Page

እንኳን ደስ አላችሁ!! የወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በዓለም አቀፍ የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ISO 9001:2015 (QMS) ተግባራዊ በማድረጉ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የጥራት ሥራ አመራር ሥርአት ሰርተፊኬት ተሰጥቶታል። ኮሌጁ የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን ማሟላቱን በተከናወነለት የኦዲት ሂደት ተገምግሞ ብቁ ሆኖ በመገኘቱ ሰርቲፊኬቱን ሊያገኝ ችሏል። የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ኢ/ር መዓዛ አበራ ለኮሌጁ የበላይ ሥራ ኃላፊዎች ሰርቲፊኬቱን አስረክበዋል፡፡ በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ኢ/ር መዓዛ አበራ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል። በዚህም ለኮሌጃችን አመራሮች፣ አሰልጣኞች፣ የአስተዳደር ሰራተኞች፣ ለኮሌጃችን ኳሊቲ ማኔጀርና ኢንተርናል ኳሊቲ ኦዲተር አባላት በልዩነት፣ ሰልጣኞች፣ የቦርድ አባላት፣ የደሴ ከተማ አስተዳደር ስራና ስልጠና መምሪያ ሀላፊዎችና ሰራተኞች፣ የአብክመ ስራና ስልጠና ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች ይህን ስኬት ለማግኘት በምናደርገው ጥረት ሁሉ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተሳትፎ ላደረጋችሁ በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን። ኮሌጃችን በየጊዜው ራሱንና አሰራሩን እያሳደገ የመጣ ታሪካዊ ኮሌጅ ሲሆን ወደፊትም በአስደማሚነቱና በታሪካዊነቱ ይቀጥላል። በድጋሜ እንኳን ደስ ያላችሁ እንኳን ደስ አለን!!

..........................................................................................................................................

Posted date:- 2025-04-22 08:24:13         Back To Main Page

የ3ኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ቀረበ ወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በቀን 06/08/2017 ዓ.ም የ3ኛ ሩብ ዓመት ስራ አፈፃፀም ሪፖርት ለአጠቃላይ የኮሌጁ ሰራተኞች የቀረበ ሲሆን በሪፖርቱ በየስራ ሂደቱ በ9ወር የተሰሩ ስራዎችን ያጋጠሙ ችግሮችን እንዲሁም የተወሰዱ መፍትሄዎችን በኮሌጃችን የዕቅድና በጀት ባለሙያ በሆኑት በአቶ ብርሀን አበራ በዝርዝር የቀረቡ ሲሆን ከዛ በመቀጠልም የኢዝ ፕሮጀክት (EASE PROJECT) አሁን የደረሰበትንና ስለ ፕሮጀክቱ አካሄድ በኮሌጃችን ዲን በአቶ ሰለሞን ይመር ሪፖርት ቀርቧል፡፡በመጨረሻም ከተሰብሳቢዎች አስተያየት እና ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን ለተነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶች ማብራሪያ በመስጠት ዉይይቱ ተጠናቋል፡፡ #WSPC PR

..........................................................................................................................................

Posted date:- 2025-04-22 08:29:36         Back To Main Page

የወ/ሮ ስኂን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የክላስተር የቴክኖሎጅ ፈጠራ ሥራዎች ውድድር አካሄደ የወ/ሮ ስኂን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2017ዓ.ም በክልልና፣በፌደራል ደረጃ ለሚካሄደው የቴክኖሎጅ የክህሎት፣ የተግባር ምርምርና የፈጠራ ሥራዎች ውድድር ላይ ለመሳተፍ በክላስተር ደረጃ በ17/07/2017ዓ.ም ውድድር አካሂዷል፡፡ በዚህም ውድድር ላይ በአሰልጣኝ፣ በሰልጣኝና በኢንተርኘራይዝ የተለያዩ ቴክኖሎጅዎችና በሰልጣኞች ብቻ የክህሎት ውድድር በ12 ሙያዎች ቀርበዋል፡፡የወ/ሮ ስኂን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ክላስተር ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ሎጐ ሃይቅ ቴ/ሙ/ኮሌጅ፣ ወገልጤና ቴ/ሙ/ኮሌጅ፣ እቴጌ መነን ቴ/ሙ/ኮሌጅ፣ ኩታበር ቴ/ሙ/ኮሌጅ ሲሆኑ ከየኮሌጆቹ የቀረቡ ቴክኖሎጅዎችና በክህሎት ተወዳድረው ላሸነፉ የምስክር ወረቀትና ሽልማት በወ/ሮ ስኂን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን በአቶ ሰለሞን ይመር ተሰጥቷል፡፡ አቶ ሰለሞን በሽልማቱ ወቅት እንደተናገሩት ቴክኖሎጅ ለአንድ ሀገር እድገት ወሳኝና ቁልፍ በመሆኑና በክህሎት የዳበሩ ሰልጣኞች አገሪቱ ስለሚያስፈልጋት ቴክኖሎጅና ፈጠራ ላይ በትኩረት እየሰራን ለኢንተርኘራይዞች ከማሸጋገር ባሻገር እንደ ገቢ ምንጭም እንጠቀምበታለን ብለዋል፡፡በዝግጅቱ ላይ የደ/ወሎ ስራና ስልጠና መምሪያ የደሴ ከተማ ስራና ስልጠና የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል፡፡

..........................................................................................................................................

Posted date:- 2025-03-17 12:52:23         Back To Main Page

ወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የኢንዱስትሪ አጋርነት ምክክር አደረገ ወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ተማሪዎች ለትብብር ስልጠና ከሚወጡባቸው ኢንዱስትሪዎች ከመጡ ባለቤቶች ጋር መጋቢት 6/2017ዓ.ም በኮምቦልቻ ከተማ ምክክር አድርጓል፡፡በውይይቱም ስለቴክኒክና ሙያ መሰረታዊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስለአዲሱ የቴክኒክና ሙያ ፖሊሲና ስትራቴጅ እንዲሁም ኢንዱስትሪዎች በትብብር ስልጠና ላይ ስለሚኖራቸው ሚና እና ሃላፊነት ስለገጽታ ግንባታ ለተሳታፊዎች ገለጻ የተደረገ ሲሆን በቀጣይም መሰራት ስላለባቸው ስራዎች ከተሳታፊዎች ለቀረቡት ሃሳቦች በውይይቱ መሪዎች ምላሽና የመፍትሄ ሃሳቦች ቀርበው ውይይቱ ተጠናቋል፡፡ #WSPC PR

..........................................................................................................................................

Posted date:- 2025-02-21 14:14:52         Back To Main Page

የአብክመ ሥራ እና ሥልጠና ቢሮ የሥራ አመራር አባላት ከተለያዩ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከመጡ ዲኖች እና ም/ዲኖች ጋር በመሆን የወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አመራሮች አሰልጣኞች እና ባለሙያዎች ISO 9001፡2015 አስመልክቶ እውቅና ለማግኘት እየሰሯቸው ያሉትን ዝርዝር ተግባራት በተመለከተ የተሞክሮና የልምድ ልውውጥ አድርገናል። በበጀት ዓመቱ ቢሮው አምስት ፖሊቴክኒኮች ኮሌጆች ማለትም ደብረብርሃን: ኮምቦልቻ : ወ/ሮ ስኂን : ጎንደር እና ባህርዳር በISO ወይም በአለም አቀፍ ስታንዳርድ ድርጅት እውቅና እንዲያገኙ እየሰራ መሆኑ ይታወቃል፡፡

..........................................................................................................................................

Posted date:- 2025-01-16 03:48:16         Back To Main Page

ለአዲስ ሰልጣኞች ኦረንቴሽን ተሰጠ፡፡ የወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለ2017 ዓ.ም አዲስ ሰልጣኞች ኦረንቴሽን ተሰጥቷል፡፡ በኦረንቴሽኑ ወቅት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሞን ይመር ብቁ ባለሙያ ለመሆን የተሟላ የስልጠና ቁሳቁስና በሙያዎች ብቁ በሆኑ አሰልጣኞች ለመሰልጠን ቴክኒክና ሙያ መምጣት አስፈላጊ በመሆኑ አማራጭ ሳይሆን ምርጫችሁ ሆኖ በሙሉ ፍላጎት በመማር አላማችሁን ማሳካት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ኦረንቴሽኑን የኮሌጁ ምክትል ዲንና የትምህርትና ስልጠና አስተባባሪ አቶ ነፃነት አሳምነው የሰጡ ሲሆን ሰልጣኞች በኮሌጁ ውስጥ ሊኖራቸው የሚገባ ስነምግባር፣ቁጠባ፣የቴ/ሙ ማሰልጠኛ ተቋም የምዘና ስርዓት እንዲሁም Ethio Coders የሚሉት ትኩረት ተደርጓባቸዋል፡፡

..........................................................................................................................................

Posted date:- 2025-01-16 03:46:21         Back To Main Page

ትምህርትና ክህሎት ለቀጣሪነት (EASE) ፕሮጀክት ድጋፍ የወይዘሮ ስኂን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሂደ። አቶ ሰለሞን ይመር የወይዘሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን የትምህርት እና ክህሎት ለቀጣሪነት (EASE)ፕሮጀክት ተግባራትን በዝርዝር እንዳቀረቡት ፕሮጀክት የሰው ሀይል ማልማት የተቋሙን መምህራን፣ ሠራተኞችና ሠልጣኞችን በቂ የሆነ ክህሎት መፍጠር፣ ተቋሙን በግብአት በማሟላት ለማገዝ የተለያዩ ማሽኖችን በቴክኖሎጅ የማዘመን ስራ ይሰራል፣ ተቋሙ ሀገር አቀፍ እና በአለም አቀፍ ደረጃ በጥራት ተወዳዳሪ ለማድረግ ይሠራል። ፕሮጀክቱ በ5 ሚሊየን ዶላር የሚተገበር ሲሆን የተቋሙን የሠው ሀይል የማብቃትና አቅም መፍጠር ላይ የሚያተኩር ነው። ፕሮጀክቱም በተቋሙ ላይ በጨርቃ ጨርቅ፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ እና በኤሌትሪክ ሰቲ ዘርፍ ላይ የትኩረት አድርጎ የሚሠራ መሆኑን የገለጹት አቶ ሠለሞን ይመር በተቋሙ ያሉ መምህራንንና ተማሪዎች በቂ የሆነ የክህሎት ስልጠና በመስጠት የበቃና ስራ ፈጣሪ የሠው ሀይል ይፈጠራል ብለዋል። ሠልጣኝ ተማሪዎችንም ለማብቃት ከተለያዩ ኢንደስትሪዎች ጋር በመመደብ እራሳቸውን በተግባር ልምምድ እንዲያበቁ ይደረጋል ብለዋል። የደሴ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ እንደገለጹት አንጋፋና በርካታ ሙህራኖችን ያፈራው የወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ተቋም የተሻለና የበቃ የሠው ሀይል በማሠልጠን በቂ የሠው ሀይል ማፍራት እና ተቋማትን በተሻለ ግብአት ማሟላት እየሠራ ስለሆነ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል። የአማራ ክልል ስራና ክህሎት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ስቡህ ገበያው ወ/ሮ ስኂን ተቋም በርካታ ሙህራኖችን በማፍራት የሚታወቀውን የቀድሞ ስሙን በመመለስ በርካታ ሙህራንችን ለማፍራት በቁጭት ልትሠሩ ይገባል። በእቅድ ትውውቅ መርሀ ግብሩ የአማራ ክልል ስራና ክህሎት ቢሮ አመራር አካላት፣ የደሴ ከተማና የደቡብ ወሎ ዞን የስራና ክህሎት መምሪያ አመራሮችና ቡድን መሪዎች፣ የወይዘሮ ስኂን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ማኔጅመንት አባላት እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

..........................................................................................................................................

Posted date:- 2025-01-16 03:45:38         Back To Main Page

በseed ፕሮጀክት አስተባባሪነት Entrepreneurship Development Institute (EDI) እና American Academy of Technology (ACT) አማካኝነት በወይዘሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡ ደሴ፡-ታህሳስ 08/2017ዓ.ም ወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ስልጠናው የቅጥር ችሎታ፣ ዲጂታል እውቀትንና የስራ ፈጠራን በተመለከተ ሲሆን Entrepreneurship Development Institute (EDI) ባዘጋጀው ስልጠና ላይ ከዚህ በፊት በሰለጠኑ የኮሌጁ አሰልጣኞች አማካኝነት እየተሰጠ ነው፡፡ በስልጠናው በግልና በመንግስት ተቋማት የሚገኙ ተመራቂ ተማሪዎችና ከየክፍለ ከተማ የተውጣጡ ስራ አጥ ወጣቶች ተሳታፊ ናቸው፡፡

..........................................................................................................................................

Posted date:- 2025-01-16 03:43:50         Back To Main Page

የISO 9001:2015 የጥራት አመራር ስርዓትን አስመልክቶ ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡ ደሴ፡-ህዳር 26/2017ዓ.ም ወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የወይዘሮ ስኂን ፖቴክኒክ ኮሌጅ የISO 9001:2015 የጥራት አመራር ስርዓትንና ካይዘንን አስመልክቶ ለሰራተኞች የተዘጋጀ የግንዛቤ ፈጠራ ስልጠና በኮምቦልቻ ከተማ እየተሰጠ ነው፡፡ ስልጠናው Education and Skill for Employment Project (EASE) ባደረገው የገንዘብ ድጋፍ አማካኝነት የሚሰጥ ሲሆን ከእሁድ ጀምሮ በመሰጠት ላይ ነው፡፡ ሰልጣኞች ከስልጠናው በኃላ ከዚህ ቀደሙ በተሻለ ስለካይዘንና ISO 9001:2015 የጥራት አመራር ስርዓትን በተመለከተ በቂ እውቀት ይይዛሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡

..........................................................................................................................................